ከፍተኛ ሊግ | ቡታጅራ ተጨማሪ ተጫዋቾች አስፈርሟል

ቀደም ብሎ በርካታ ተጫዋቾችን ማስፈረም የቻለው ቡታጅራ ከተማ ሁለት ተጨማሪ ተጫዋቾችን ወደ ቡድኑ ቀላቅሏል።

ሙሉነህ ጌታነህ ከፈረሙት መካከል ነው። በቶም ሴንትፌት አሰልጣኝነት ዘመን የኢትዮጵያ ብሄራዊ ቡድን አባል የነበረው ሙሉነህ በክለብ ደረጃ በመከላከያ፣ ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ፣ ዳሽን ቢራ፣ ወልዲያ እና ኮምቦልቻ የተጫወተ ሲሆን በ2011 በቡራዩ ከተማ አሳልፏል።

ሁለተኛው ፈራሚ ድንቅነህ ከበደ ነው። በሀምበሪቾ ጥሩ የውድድር ጊዜ ማሳለፉን ተከትሎ በአሰልጣኝ ፖፓዲች ለኢትዮጵያ ቡና ፈርሞ ኋላ ላይ በውሰት ውል ለአዲስ አበባ ከተማ የተጫወተው ድንቅነህ ያለፈውን ዓመት በቢሾፍቱ ከተማ አሳልፏል።

ቡታጅራ ከተማ በዘንድሮ ዓመት ጠንካራ ተፎካካሪ ሆኖ ለመገኘት የ13 ተጨዋቾችን ውል ከማደሱ በተጨማሪ 11 አዲስ ተጨዋቾችን አስፈርሟል።


© ሶከር ኢትዮጵያ