ከፍተኛ ሊግ | ሀምበሪቾ ስምንት አዳዲስ ተጫዋቾች ወደ ቡድኑ ቀላቅሏል

በአሰልጣኝ ዓለማየሁ ዓባይነህ እየተመራ ባለፈው ዓመት በተሳተፈበት የከፍተኛ ሊግ ምድብ ለ አራት ጨዋታ እስከሚቀረው ድረስ ወደ ፕሪምየር ሊግ ለማደግ ሲፎካከር የነበረው ሀምበሪቾ ለዘንድሮው የውድድር ዘመን በርካታ ነባር ተጫዎቾችን ውል ሲያድስ ሰባት ተጫዋቾች ወደ ቡድኑ ቀላቅለዋል።

በአጥቂ ስፍራ ላይ ላለፉት ሦስት ተከታታይ ዓመታት ጥሩ ብቃት ያሳየው ቴዲ ታደሰ ወደ ቀድሞ ቡድኑ ተመልሷል። ተጫዋቹ ባለፈው ዓመት ከሀምበሪቾ ወደ አርባምንጭ አምርቶ የተጫወተ ሲሆን በክረምቱ ወደ ደቡብ ፖሊስ ለማምራት ተስማምቶ የነበረ ቢሆንም ማረፊያውን የቀድሞ ቡድኑ አድርጓል።

ዳግም በቀለ ሌላው ክለቡን የተቀላቀለ ተጫዋች ነው። የቀድሞው የነገሌ ቦረና እና ወላይታ ድቻ ባለፈው ዓመት በሀዲያ ሆሳዕና ቆይታ የነበረው ሲሆን ቡድኑ ወደ ፕሪምር ሊግ እንዲያድግ አስተዋፅኦ አበርክቷል።

ተስፋዬ በቀለ ቡድኑን የተቀላቀለ ተጫዋች ሆኗል። ወጣቱ የመስመር ተጫዋች ከቅዱስ ጊዮርጊስ ወደ ወልቂጤ ካመራ በኋላ ያለፈውን ዓመት ወደ ፕሪምየር ሊግ ባደገው ቡድን ውስጥ ሲጫወት ቆይቷል።

የከምባታ ሺንሺቾ አጥቂ ናሆም አምሮ ወደ ሀምበሪቾ ካመሩት ውስጥ ሆኗል። ናሆም በተለይም በሁለተኛው ዙር በተከታታይ የ
በሚስቆጥራቸው ግቦች ቡድኑን በተጋጋሚ ሲታደግ ታይቷል።

በአማካይ ስፍራ መሳይ አገኘው ከወላይታ ሶዶ፣ አስጨናቂ ፀጋዬ ከአርባ ምንጭ ከተማ፣ ፊንሀስ ተገኝ ከሆሳዕና እንዲሁም ወላይታ ድቻ እና ሀድያ ሆሳዕና ወደ ፕሪምየር ሊግ ሲያድጉ ጥሩ ግልጋሎት ሲሰጥ የነበረው ሙሉነህ ገብረመድህን ወደ ሀምበሪቾ ያመሩ ሌሎችተጫዎቾች ናቸው።

ቡድኑ ከነባሮቹ መካከል የ17 ተጫዋቾችን ውል በማደስ በአጠቃላይ 24 ተጫዋቾችን ይዞ በዱራሜ ከተማ የቅድመ ውድድር ዝግጅቱን በቅርብ ቀን እንደሚጀምር ቡድኑ አሳውቋል።


© ሶከር ኢትዮጵያ