ዋልያዎቹ በመቐለ ልምምዳቸውን ጀምረዋል

በአፍሪካ ዋንጫ ማጣርያ የመጀመርያ ጨዋታቸውን ለማድረግ በዝግጅት ላይ የሚገኙት ዋልያዎቹ በመቐለ ልምምዳቸውን ጀምረዋል።

ከማዳጋስካር እና አይቮሪኮስት ጋር ለሚያደርጓቸው የአፍሪካ ዋንጫ ማጣርያ ጨዋታዎች ከጥቂት ቀናት በፊት ጥሪ የተደረገላቸው ዋልያዎቹ በትናንትናው ዕለት ከአዲስ አበባ ወደ ከተማው በማቅናት በአስር ሰዓት ቀለል ያለ ልምምድ የጀመሩ ሲሆን በዛሬው ዕለትም አራት ሰዓት እና አስር ሰዓት ሁለት ልምምዶች ሲሰሩ የብሄራዊ ቡድኑ አምበል ሽመልስ በቀለም በዛሬው ዕለት ቡድኑን ተቀላቅሏል።

ሌላው ከግብፁ ሃራስ ኤል ሁዱድ ጥሪ የተደረገለት ጋቶች ፓኖም አመሻሹን መቐለ መግባቱ ሲታወቅ ነገ ከቡድኑ ጋር ልምምድ ይጀምራል ተብሎ ይጠበቃል። ከቀናት በፊት በስዊድን ሱፐርታን ሊግ ጨዋታ ያደረገው ቢንያም በላይም በቀጣይ ቀናት ቡድኑ ይቀላቀላል ተብሎ ይገመታል።

ለካሜሩን አፍሪካ ዋንጫ ከአይቮሪኮስት ፣ ማዳጋስካር እና ኒጀር ጋር የተደለደለው የኢትዮጵያ ብሄራዊ ቡድን የመጀመርያ ጨዋታውን ወደ አንታናሪቮ አቅንቶ ማዳጋስካርን ሲገጥም ከቀናት በኃላም በትግራይ ስታዲየም አይቮሪኮስትን ይገጥማል።


© ሶከር ኢትዮጵያ