ከፍተኛ ሊግ | የደሴ ከተማ ተጫዋቾች ላቀረቡት ቅሬታ ክለቡ ምላሽ እንዲሰጠው ፌዴሬሽኑ ጠየቀ

ፌዴሬሽኑ ደሴ ከተማ ቀሪ የውል ዓመት ያላቸው አራት ተጫዋቾችን ስለመልቀቁ በአስር ቀን ውስጥ ማብራርያ እንዲሰጠው አሳስቧል፡፡

በከፍተኛ ሊጉ ተሳታፊ በሆነው ደሴ ከተማ ዐምና ይጫወቱ የነበሩ አራት ተጫዋቾች ማለትም ሚሊዮን በየነ፣ ኃይለማሪያም እሸቱ፣ ዓለማየሁ ማሞ እና ሊቁ አልታዬ ዘንድሮ በክለቡ የሚያቆያቸው የሰባት እና የስድስት ወራት የውል ቆይታ እያላቸው ክለቡ ግን ተጫዋቾቹን ከስብስቡ ውጪ ማድረጋቸውን ተጫዋቾቹ ለሦስት ጊዜያት ለፌዴሬሽኑ ባስገቡት ደብዳቤ አቤቱታቸውን አሰምተዋል።

በዚህም መሠረት የፌዴሬሽኑ የዲሲፕሊን ኮሚቴ ተጫዋቾቹ የውል ጊዜ እያላቸው ከክለቡ መሰናበታቸውን በመግለፅ “ክለቡ በአስር ቀናት ውስጥ አፋጣኝ ምላሽ ይስጠኝ” ሲል አሳስቧል፡፡


© ሶከር ኢትዮጵያ