ከፍተኛ ሊግ | ለገጣፎ ሰባት ተጨማሪ ተጫዋቾች ወደ ቡድኑ ቀላቅሏል

በአሰልጣኝ ዳዊት ሀብታሙ እየተመራ ዝግጅቱን በባቱ ከተማ እያደረገ የሚገኘው ለገጣፎ ለገዳዲ ሰባት ተጨማሪ ተጫዋቾች ማስፈረም ችሏል።

በተከላካይ ስፍራ ላይ የሚጫወተው የቀድሞ የቅዱስ ጊዮርጊስ እና የኢትዮ ኤክትሪክ ተጫዎች ዘካርያስ ቱጂ ወደ ለገጣፎ ካመሩት መካከል ነው። ሌላው በተከላካይ ስፍራ የሚጫወተውና በአዳማ እና በድቻ ተጫውቶ ያሳለፈው ወንድወሰን ቦጋለ ወደ ለገጣፎ አምርቷል።

በዘንድሮ ውድድር ዓመት ኢትዮጵያ ቡና ተቀላቅሎ ኋላ ላይ የተለያየው እና በወልቂጤ የቡድኑ አምበል ሆኖ ቡድኑ ወደ ፕሪምየር ሊግ እንዲያድግ አስተዎፆ ያበረከተው ብስራት ገበየሁ ወደ ለገጣፎ ያመራ ሲሆን እንደብስራት ሁሉ ሰበታ ከተማ ሲያድግ ጉልህ አስተዎፅ ያደረገው የቀድሞ የዳሽን ቢራ፣ ወላይታ ድቻ እና ጅማ አባ ቡና ሁለገብ ተጫዋች ኃይልእየሱስ ብርሃኑ እንዲሁም የቀድሞ ሀረር ቢራ፣ የአክሱም እና የገላን ተጫዎች የነበረው አብዱራሂም ሙስጣፋ በአማካይ ስፍራ ቡድኑ የተቀላቀሉ ተጫዋቾች ናቸው።

ግብ ጠባቂው ሚሊዮን አበራ ሌላው የለገጣፎ አዲስ ፈራሚ ነው። ሚሊዮን ከዚህ ቀደም በሱልልታ፣ አዲስ አበባ ፖሊስ እና ቢሾፍቱ አውቶሞቲቭ ተጫውቷል።

ቡድኑ ከታዳጊ ቡድን ወደ ዋናው ቡድን በግብ ጠባቂ ስፍራ ላይ ዳግም አምደስላሴን ያሳደገ ሲሆን በተጨማሪም የአስራ አራት ተጫዋቾችን ውል አድሷል።


© ሶከር ኢትዮጵያ