የኢትዮጵያ እና አይቮሪኮስት ጨዋታ የስታዲየም ለውጥ ተደርጎበታል

የዋልያዎቹ ጨዋታ የስታዲየም ለውጥ ተደርጎበታል።

ኢትዮጵያ እና አይቮሪኮስት የሚያደርጉት የአፍሪካ ዋንጫ ሁለተኛ የማጣርያ ጨዋታ መቐለ ላይ ሊካሄድ መርሐ ግብር ወጥቶለት እንደነበር ሲታወስ ካፍ በወሰነው መሰረት የስታዲየም ለውጥ ተደርጎበታል። በዚህም ታህሳስ 9 የሚካሄደው ጨዋታ ከትግራይ ስቴድየም ወደ ባህርዳር ስቴድየም ለውጥ ተደርጎበታል።

ካፍ የስቴድየም ለውጥ እንዲደረግ ያዘዘበት ምክንያት ባይታወቅም ከቀናት በፊት ስታድየሞቹን ተዟዙሮ ካየ በኃላ የወሰነው ከምዘናው መነሻነት ጋር የተያያዘ ምክንያት ሊሆን እንደሚችል ይገመታል።


© ሶከር ኢትዮጵያ