የሴካፋ ሴቶች ዋንጫ የሚጀመርበት ቀን ሽግሽግ ተደረገበት

በታንዛኒያ አስተናጋጅነት የሚከናወነው የ2019 ሴካፋ ሴቶች ዋንጫ የሚጀመርበት ጊዜ በሁለት ቀናት ተሸጋሽጓል፡፡

ኖቬምበር 14 (ኅዳር 4) ይጀመራል ተብሎ የነበረው ውድድሩ ከሁለት ቀናት በኋላ ቅዳሜ ኅዳር 6 (ኖቬምበር 16) የሚጀምር ሲሆን የቀን ሽግሽጉ ምክንያት ይፋ አልተደረገም፡፡

የኢትዮጵያ ሴቶች ብሔራዊ ቡድን ለውድድሩ ከሳምንቱ መጀመርያ አንስቶ ልምምድ እያደረገ የሚገኝ ሲሆን በነገው ዕለትም ከኢትዮጵያ ወጣቶች ስፖርት አካዳሚ ከ15 ዓመት በታች ወንዶች ቡድን ጋር የአቋም መለኪያ ጨዋታ በአዲስ አበባ ስታዲየም ረፋድ 4፡00 ላይ እንደሚያደርግ ፌዴሬሽኑ አስታውቋል፡፡

ሉሲዎቹ በሴካፋ ውድድር ከኬንያ፣ ዩጋንዳ እና ጅቡቲ ጋር መደልደሏ ይታወቃል፡፡


© ሶከር ኢትዮጵያ