2021 አፍሪካ ዋንጫ| ዋልያዎቹ ነገ ወደ አንታናናሪቮ ያቀናሉ

ዋልያዎቹ ዛሬ በመቐለ የመጨረሻ ልምምዳቸው አከናውነዋል።

በአፍሪካ ዋንጫ ማጣርያ ማዳጋስካርን ለመግጠም በመቐለ ዝግጅት እያደረጉ የቆዩት ዋልያዎቹ ዛሬ በመቐለ የመጨረሻ ልምምዳቸው ሰርተው አመሻሹ አዲስ አበባ ገብተዋል። ወደ አንታናሪቮ አቅንተው ጠንካራዋን ማዳጋስካር የሚገጥሙት ዋልያዎቹ ላለፉት ሳምንታት ጠንካራ ዝግጅት እያደረጉ መቆየታቸው ሲታወስ ሙሉ ቡድኑም በጥሩ ጤንነት እንደሚገኝ ለማወቅ ተችሏል።

ከአዲስ አበባ ወደ አንታናናሪቮ የሚደረገው በረራ በሳምንት አንድ ጊዜ በመሆኑ ቀድመው በነገው ዕለት ወደ ስፍራው የሚያቀኑት ዋልያዎቹ የማጣርያው የመጀመርያ ጨዋታቸው በመሐማሲና ሙንሲፓል ስቴድየም ማዳጋስካርን ሲገጥሙ ከሶስት ቀናት በኃላም በትግራይ ስቴድየም አይቮሪኮስትን የሚገጥሙ ይሆናል።

የኢትዮጵያ ብሄራዊ ቡድን የአፍሪካ ዋንጫ ማጣርያ ጨዋታዎች

ማዳጋስካር ከ ኢትዮጵያ
አንታናናሪቮ
ኖቬምበር 16 2019

ኢትዮጵያ ከ አይቮሪኮስት
መቐለ
ኖቬምበር 19 2019

ኒጀር ከ ኢትዮጵያ
ቦታ አልታወቀም
ኦገስት 31 2020

ኢትዮጵያ ከ ኒጀር
ቦታ አልታወቀም
ሴፕተምበር 8 2020

ኢትዮጵያ ከ ማዳጋስካር
ቦታ አልታወቀም
ኦክቶበር 5 2020

አይቮሪኮስት ከ ኢትዮጵያ
ቦታ አልታወቀም
ኖቬምበር 9 2020


© ሶከር ኢትዮጵያ