የሴካፋ ወንዶች ብሔራዊ ቡድን ውድድር በቅርቡ ይካሄዳል

በሁለቱም ፆታዎች በተለያዩ የዕድሜ እርከኖች በርከት ያሉ ውድድሮችን በማካሄድ ላይ የሚገኘው ሴካፋ በዚህ ወር መጨረሻ የወንዶች ብሔራዊ ቡድን ውድድር ያካሄዳል።

ከኀዳር 27 – ታህሳስ 9 ቀን ድረስ በሚካሄደው በዚህ ውድድር የተሳታፊ ሀገራት ዝርዝር ለጊዜው ባይታወቅም ውድድሩን ዩጋንዳ እንደምታዘጋጅ ተረጋግጧል። በዚህ ውድድር ላይ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን እንደሚሳተፍ ሲታወቅ ከሁለት የአፍሪካ ዋንጫ ማጣርያ ጨዋታዎች በኋላ የቀናት እረፍት በማድረግ ለሴካፋው ውድድር ዝግጅት እንደሚጀምር ይጠበቃል።

ያለፉትን ዓመታት በተለያዩ ምክንያቶች አንዴ ሲካሄድ ሌላ ጊዜ እየተቋረጠ የቀጠለው የሴካፋ ውድድር ዘንድሮ በአዲስ አቀራረብ ውድድሩን ለማካሄድ ቅድመ ዝግጅቱን እያጠናቀቀ መሆኑን ሰምተናል።


© ሶከር ኢትዮጵያ