ከፍተኛ ሊግ | አክሱም ከተማ የሰባት ተጫዋቾች ዝውውር አጠናቀቀ

በትግራይ ዋንጫ ጥሩ ብቃት እያሳዩ የሚገኙት አክሱም ከተማዎች ተጨማሪ ሰባት ተጫዋቾችን ወደ ቡድናቸው ቀላቅለዋል።

በዝውውር መስኮቱ መጀመርያ አሰልጣኝ ዳንኤል ፀሃዬ እና ምክትሉ ይድነቃቸው ዓለሙን ጨምሮ በርካታ ተጫዋቾች ያስፈረሙት አክሱሞች አሁን ደግሞ የቀድሞ የደደቢት እና የስሑል ሽረ አማካይ አሸናፊ እንዳለ፣ የቀድሞ የመድን እና ቡራዩ የመስመር ተከላካይ ዮሃንስ ዓፈራ፣ ከዚህ ቀደም በመቐለ እና ቡራዩ የተጫወተው ግብ ጠባቂው አሸብር ደምሴ፣ አጥቂው ዮሐንስ አድማሱ፣ ተከላካዩ ግዮን መላኩ፣ አማካዩ አዲስዓለም ደሳለኝ እና ከዚህ ቀደም በኢትዮጵያ ቡና፣ ዳሽን ቢራ እና ኢኮስኮ የተጫወተው ሳሙኤል ወንድሙ አስፈርመዋል።

በትግራይ ዋንጫ ጥሩ ብቃት በማሳየት በውድድሩ ወደ ቀጣዩ ዙር ማለፋቸው ያረጋገጡት አክሱሞች ከላይ የተጠቀሱትን አዲስ ፈራሚዎች በውድድሩ ላይ እየተጠቀሙባቸው ሲሆንበቀጣይ ዓመት በከፍተኛ ሊጉ ጠንካራ ቡድን ይዘው ለመቅረብ በዝግጅት ላይ ይገኛሉ።


© ሶከር ኢትዮጵያ