ኢትዮጵያ ቡና ከ ዳሽን ቢራ ፡ ቅድመ ጨዋታ ዳሰሳ

 

ዛሬ ከተቋረጠበት የቀጠለው የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ነገ የኢትዮጵያ ቡና እና ዳሽን ቢራን ጨዋታ ያስተናግዳል፡፡ የፕሪሚየር ሊጉ ጨዋታ በዘንድሮው የውድድር ዘመን ለመጀመርያ ጊዜ ወደ አበበ ቢቂላ ሲያመራ በ10፡00 ጨዋታው ይደረጋል፡፡ ዛሬ ኤሌክትሪክ እና ንግድ ባንክ በማሸነፋቸው ወደ 11ኛ ደረጃ ያሽቆለቆለው ኢትዮጵያ ቡና ከወራጅ ቀጠና የመውጣት አላማን ሰንቆ ዳሽን ቢራን ያስተናግዳል፡፡

በውዝግብ እና ወጥ ባልሆነ አቋም ወደ 1 ወር እረፍት ያመራው ኢትዮጵያ ቡና ክፍተቶቹን የመድፈኛ በቂ ጊዜ አግኝቷል፡፡ አሰልጣኝ ድራጋን ፖፓዲች ተጨማሪ ሶስት ተጫዋቾችን በማስፈረም ዝግጅታቸውን ያደረጉ ሲሆን የወዳጅነት ጨዋታም ማድረግ ችለዋል፡፡

በነገው ጨዋታ በኢትዮጵያ ቡና በኩል ጋቶች ፓኖም በቻን ባጋጠመው ጉዳት ምክንያት አይሰለፍም፡፡ ለረጅም ጊዜ በጉዳት ያልተሰለፈው ግብ ጠባዊው ሃሪሰን ሆውሲ ከጉዳቱ ቢያገግምም ለጨዋታ ብቁ ለመሆን ተጨማሪ ቀናት የሚፈልግ በመሆኑ የነገውን ጨዋታ የማድረግ እድሉ አጠራጣሪ ነው፡፡ አዲስ ፈራሚዎቹ ንዳዬ ፋይስ እና ፓትሪክ ኦኮሌ የአለም አቀፍ ዝውውር ሰርፍኬት ያልተጠናቀቀላቸው በመሆኑ ቡና በነገው ጨዋታ የካሜሩናዊያኑን አጥቂዎች ግልጋሎት አያገኝም፡፡ ሌላው አዲስ ፈራሚ ኤርሚያስ በለጠ ግን ዝውውሩ ሙሉ ለሙሉ በመጠናቀቁ ነገ ለመሰለፍ ብቁ ነው፡፡

ጥሩ የውድድር ዘመን ጅማሬ አድርጎ መንሸራተት ያሳየው ዳሽን ቢራ ወደ አሸናፊነት በተመለሰበት ወቅት ሊጉ በድጋሚ ተቋርጧል፡፡ ከሊጉ መቋረጥ በፊት ኤሌክትሪክን ያሸነፈው ዳሽን ቢራ ከ1 ወር እረፍት ውስጥ ለዝግጅት የተጠቀመው ዘጠኙን ቀን ብቻ እንደሆነ ታውቋል፡፡ አሰልጣኝ ታረቀኝ አሰፋ ግን ባላቸው አጭር ጊዜ ውስጥ ቡድናቸውን ለፕሪሚየር ሊጉ እንዳዘጋጁ ለሶከር ኢትዮጵያ ተናግረዋል፡፡

ከዳሽን ቢራ በኩል ከአስራት ውጪ ሁሉም ተጫዋቾች ለጨዋታው ብቁ የሆኑ ሲሆን አስራት መገርሳ በቻን ውድድር ባስተናገደው ጉዳት ምክንያት ህክምና እየተከታተለ ይገኛል፡፡

ያለፉት 5 ጨዋታዎች ውጤቶች

ኢትዮጵያ ቡና ፡ አቻ – አሸነፈ – አቻ – ተሸነፈ – ተሸነፈ

ዳሽን ቢራ ፡ ተሸነፈ – አቻ – ተሸነፈ – ተሸነፈ – አሸነፈ

 

የእርስ በእርስ ግንኙነቶች

ዳሽን ቢራ በ2006 ወደ ሊጉ ካደገ ወዲህ ሁለቱ ቡድኖች ባደረጉት 4 ጨዋታ ዮንደሩ ክለብ ድል ማግኘት አልቻለም፡፡ ኢትዮጵያ ቡና ሶስት ጨዋታዎች በማሸነፍ ዳሽን ቢራ ላ የበላይነትን ይዟል፡፡

Bunna Dashen Fact

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *