የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ የሚጀመርበት ቀን በአንድ ሳምንት ተራዝሟል

ዛሬ በአዳማ እየተደረገ ባለው የዕጣ ማውጣት ሥነ-ስርዓት ፕሪምየር ሊጉ በአንድ ሳምንት ተገፍቶ እንደሚጀመር ተገለፀ፡፡

የ2012 የኢትዮጵያ ፕሪምየር ህዳር 13 እንደሚጀመር አስቀድሞ ይፋ የተደረገ ቢሆንም ትላንት ደግሞ ለማራዘም እንደተወሰነና ዛሬ መቼ እንደሚጀምር ውሳኔ እንደሚሰጥበት መዘገባችን ይታወሳል፡፡ ዛሬ በአዳማ ኤክስኪዩቲቭ ሆቴል 9:30 በጀመረው የዕጣ ማውጣት እና በደንቦች ዙሪያ እየተደረገ ባለው ውይይት ላይም ሊጉ ከህዳር 21 እስከ ሰኔ 15 ድረስ ለማድረግ መወሰኑን አዲስ የተቋቋመው የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ ውድድር እና ሥነ-ስርዓት ኮሚቴ ሰብሳቢ ወገኔ ዋልተንጉስ (ዶ/ር) ይፋ አድርገዋል፡፡


© ሶከር ኢትዮጵያ