ማዳጋስካር ከሜዳዋ ውጪ ኒጀርን ረመረመች

ኢትዮጵያ በምትገኝበት ምድብ 11 የተደለደሉት ኒጀር እና ማዳጋስካርን ያገናኘው ጨዋታ በማዳጋስካር ስድስት ለሁለት አሸናፊነት ተጠናቋል።

በኒጀር ስታደ ሰይኒ ኮይንቼ ስቴድየም በተካሄደው ጨዋታ ባለሜዳዎቹ ኒጀሮች በስድስተኛው ደቂቃ በዎንኮየ አማካኝነት ባስቆስጠሯት ጎል መምራት ቢችሉም ማዳጋስካሮች በኖሜንጃናህ (2) ፣ አኒሰንት አቤል፣ አንድርያማሂትስ፣ ፓውሊን ቮአቭይ እና ሞምብሪስ በተቆጠሩ ስድስት ግቦች ባለሜዳዎቹን ስድስት ለሁለት ማሸነፍ ችለዋል ፤ የኒጀር ሁለተኛ ግብም ሞሳ በሰባ ሰባተኛው ደቂቃ ላይ ማስቆጠር ችሏል።

ይህንን ተከትሎም ኢትዮጵያ እና ኒጀርን ያሸነፈችው ማዳጋስካር በስድስት ነጥብ እና በአምስት የግብ ክፍያ ምድቡን ስትመራ ኢትዮጵያ እና አይቮሪኮስት በእኩል ሶስት ነጥብ እና በባዶ የግብ ክፍያ ይከተላሉ። ተከታታይ ሽንፈት ያስተናገደችው ኒጀር በባዶ ነጥብ እና በአምስት የግብ ዕዳ የምድቡን የመጨረሻ ደረጃ ይዛለች።

የምድቡ ቀጣይ መርሃ ግብር ኦገስት 13 (ነሀሴ 7) ሲደረግ ኒጀር እና ኢትዮጵያ በኒጀር ኒያሜ እንዲሁም ማዳጋስካር እና አይቮሪኮስት በማዳጋስካር አንታናናሪቮ ይፋለማሉ።


© ሶከር ኢትዮጵያ