ሳላዲን ሰዒድ ዳግም ወደ ብሔራዊ ቡድን ሊመለስ ነው

በአአ ከተማ ዋንጫ ዳግም የተወለደው አንጋፋው አጥቂ ሳላዲን ሰዒድ ዳግም ወደ ብሔራዊ ቡድን ሊመለስ እንደሚችል አሰልጣኝ አብርሀም መብራቱ ተናገሩ።

ዋልያዎቹ በተለይ በፊት መስመር ላይ የሚታይባቸውን ተደጋጋሚ የማጥቃት እንቅስቃሴያቸው መዳከምን ለመቅረፍ በአአ ከተማ ዋንጫ ምርጥ አቅሙን እያሳየ የሚገኘው ሳላዲን ሰዒድ ወደ ብሔራዊ ቡድኑ ቢጠራ መልካም ነው የሚል ተደጋጋሚ ጥያቄዎች በስፖርት ቤተሰቡ ዘንድ ሲነገር ቆይቷል። ይህን ተከትሎ ጥያቄ የቀረበላቸው የዋልያዎቹ አለቃ አብርሀም መብራቱ ይህን ብለዋል።

” ወደ ማዳጋስካር ከማቅናታችን በፊት ልምድ ያለው ተጫዋች እንደሚያስፈልገን አምነንበት ነበር። ለዛም ከሳላዲን ጋር ተነጋግረናል፣ ሆኖም ለጨዋታ ያለው ዝግጅት ገና በመሆኑ ትንሽ ጊዜ መስጠት አስፈላጊ እንደሆነ ተማምነናል። በስነ ልቦናው ረገድ ድንገት ለብሔራዊ ቡድን ጥሪ ሲቀርብለት ዝግጁ ለመሆን ጊዜ የሚያስፈልገው በመሆኑ እንጂ በቀጣይ ሳላዲን የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ስብስብ ይቀላቀላል። ከእርሱም ጋር ተነጋግረን ጨርሰናል። አሁን የምንፈልገው የእርሱን ሙሉ ጤንነት እና ወደ መልካም ብቃቱ እንዲመጣ ብቻ ነው። ”


© ሶከር ኢትዮጵያ