ከፍተኛ ሊግ | ቤንች ማጂ ቡና አዳዲስ 12 ተጫዋቾችን አስፈርሟል

የከፍተኛ ሊግ ምድብ ሐ ተወዳዳሪው ቤንች ማጂ ቡና በ2012 የውድድር ዘመን ጠንካራ ተፎካካሪ ሆኖ ለመቅረብ ራሱን እያጠናከረ ይገኛል፡፡

የዋና አሰልጣኙ ወንዳየሁ ኪዳኔ እና የምክትሉ አበራ ገብሬን ውል በማደስ ስራውን የጀመረው ክለቡ 13 ነባር ተጫዋቾችን ውል በማደስ 12 አዳዲስ ተጫዋቾችን ወደ ክለቡ መቀላቀል ችሏል። በዚህም መሠረት፡-

አዲስ የተቀላቀሉ ተጫዋቾች

ሙሴ እንዳለ (አጥቂ ከቢሾፍቱ ከነማ)፣ ኤሊያስ እንድሪያስ (አጥቂ  ከዲላ ከተማ)፣ አካሉ አቲሞ (ተከላካይ ከአምቦ ከተማ)፣ ሙሉቀን አሰፋ (አማካይ ከቡታጅራ ከተማ)፣ ሮቤል ግርማ (ተከላካይ ከጂማ  አባቡና)፣ አቤኔዘር አስራት (አማካይ ከካምባታ ሺንሺቾ)፣ ዲንግ ኪር (ተከላካይ ከካፋ ቡና)፣ ደረጀ አበራ (አማካይ ከለገጣፎ ለገዳዲ)፣ ምስጋናው መኮንን (አጥቂ ከጂማ አባቡና)፣ ኦኒ ኡጁሉ (አጥቂ ከካፋ ቡና)፣ ሀቁምንይሁን ገዛኸኝ (የተካላካይ አማካይ ከአማራ ውሀ ስራ)፣  ስለሺ መኮንን (አማካይ ከሚዛን)

ውል ያደሱ ተጫዋቾች
ቶማስ እሸቱ (ተከላካይ)፣ ጌታሁን ገላዬ (ተከላካይ አማካይ )፣ በእውቀቱ ማሞ (ተከላካይ)፣ ቱፋ ተሸቴ (ተከላካይ)፣ ሰመረዲን እስማኤል (ተከላካይ)፣ ፎሳ ሳንዴቦ (አጥቂ)፣ ቶማስ ዘገየ (ግብ ጠባቂ)፣ ሌሊሳ ታዬ (ግብ ጠባቂ)፣ ተዘራ ጌታቸው (አጥቂ)፣ ብሩክ ወንዴ (አማካይ)፣ አዲሱ ያሉባብ (አማካይ)፣ ዳግም ኬራ (ግብ ጠባቂ) ያሬድ አማረ (ተከላካይ)


© ሶከር ኢትዮጵያ