አዳማ ከተማ ከ ሲዳማ ቡና፡ ቅድመ ጨዋታ ዳሰሳ

በ8ኛው ሳምንት ከመዲናዋ ውጪ በሚደረገው ብቸኛ ፍልሚያ የአሰልጣኝ አሸናፊ በቀለ አዳማ ከተማ መሪነቱን ለማስጠበቅ ነገ የዘላለም ሽፈራው ሲዳማ ቡናን ይገጥማል፡፡ ከመሪው በደረጃ ብዙም ያልራቀው ሲዳማ ቡናም ይበልጥ ለመጠጋት ለተጋጣሚ የሲኦል ያህል አስቸጋሪ እየሆነ የመጣው የአዳማ አበበ ቢቂላ ስታድየምን ይጎበኛሉ፡፡   

ከ7 ጨዋታዎች በአንዱ አቻ ከመውጣቱ በቀር ሁሉንም ያሸነፈው አዳማ ከተማ በሜዳው እያሳየ የሚገኘውን የበላይነት ያስጠብቃል ተብሎ ቢጠበቅም ከረጅም እረፍት በኋላ ወደ ውድድር መምጣቱ በቡድኑ ላይ የነበረውን አስደናቂ የአሸናፊነት ስነልቦና እንዳይሸረሽር ያሰጋል፡፡

በነገው ጨዋታ አዳማ ከተማ ዘንድሮ ድንቅ አቋማቸውን እያበረከቱ የሚገኙትን አማካዮቹ ብሩክ ቃልቦሬ እና ወንድወሰን ሚልኪያስን ግልጋሎት አያገኝም፡፡ በብሄራዊ ቡድን የቻን ዝግጅት ወቅት የተጎዳው ተከላካዩ ሞገስ ታደሰ ደግሞ ከጉዳቱ በማገገሙ ነገ የቀድሞ ክለቡን ለመግጠም ዝግጁ ሆኗል፡፡

አሰልጣን ዘላለም ሽፈራው በመኪና አደጋ ከደረሰበት ጉዳት አገግሞ ወደ ሲዳማ ቡና አሰልጣኝነት ከተመለሰ ወዲህ የይርጋለሙ ክለብ እየተሸሻለ ይገኛል፡፡ አሰልጣኝ ዘላለም ከተመለሱ ወዲህ ባደረጋቸው 5 ጨዋታ ያልተሸነፈው ሲዳማ ከአምናው የውድድር ዘመን አጋማሽ ጀምሮ ከገጠመው የውጤት ቀውስ ቀስ በቀስ እያገገመም ይገኛል፡፡

ሲዳማ ቡና የመስመር አማካዩ እንዳለ ከበደን እና የተከላካይ አማካዩ ቢንያም አድማሱን በጉዳት ለነገው ጨዋታ የማያሰልፍ ሲሆን የግብ ጠባቂው ለአለም ብርሃኑ እና አማካዩ ፍፁም ተፈሪ ከጉዳት ሙሉ ለሙሉ አገግሞ ወደ ጨዋታ መመለስ ለአሰልጣኝ ዘላለም ሽፈራው እፎይታን ፈጥሯል፡፡ በኢትዮጵያ ያለው የስራ ፈቃድ ተጠናቆ የነበረው ኬንያዊው አንጋፋ ኤሪክ ሙራንዳ ፍቃዱ የታደሰለት በመሆኑ በነገው ጨዋታ ላይ መሰለፍ ይችላል፡፡

ያለፉት 5 ጨዋታዎች አቋም

አዳማ ከተማ ፡ አቻ – አሸነፈ – አሸነፈ – አሸነፈ – አሸነፈ

ሲዳማ ቡና ፡ አሸነፈ – አቻ – አሸነፈ – አቻ – አሸነፈ

 

የእርስ በእስር ግንኙነቶች

ሁለቱ ክለቦች ከ2002 ጀምሮ ለ10 ጊዜያት የተገናኙ ሲሆን ሲዳማ 4 ጨዋታዎች ላይ ድ በማድረግ የተሸለ የበላይነት ይዟል፡፡ አዳማ ከተማ ሶስት ጊዜ ያሸነፈ ሲሆን ሁለቱ ድሎች የተገኙት በ2007 የውድድር ዘመን ነው፡፡

Adama Sidama Facts

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *