ዋልያዎቹ ሽልማት ተበረከተላቸው

በአፍሪካ ዋንጫ ማጣሪያ ትናንት በባህር ዳር አለም አቀፍ ስታዲየም አይቮሪኮስትን 2-1 ያሸነፈው የብሔራዊ ቡድኑ ስብስብ ከደቂቃዎች በፊት አዲስ አበባ ሲገባ አቀባበል ከተደረገለት በኋላ የምሳ ግብዣ እና የገንዘብ ሽልማት ተበርክቶለታል፡፡

የኢፌዴሪ ስፖርት ኮሚሽን ኮሚሽነር አቶ ኤልያስ ሽኩር፣ የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌድሬሽን ፕሬዝዳንት አቶ ኢሳይያስ ጅራ፣ የኢትዮጵያ አየር መንገድ ተወካዮች እና የፌዴሬሽኑ ስራ አስፈፃሚ አባላት የዋልያዎቹ የአቀባበል ስነ-ስርዓት ላይ ከታደሙ በኋላ በስካይ ላይት ሆቴል በተደረገው የምሳ ግብዣ እንዲሁም የሽልማት ፕሮግራም በመገኘት ሽልማትን አበርክተዋል፡፡

በመርሐ ግብሩ ለአልለል አብርሀም መብራቱ 35,000 ብር፣ ለረዳቶቹ 25,000 ብር፣ በትላንትናው ጨዋታ የመጀመርያ ተሰላፊ ለነበሩ 25,000 ብር፣ ለተቀሩት የቡድኑ አባላት ደግሞ የ20,00 ሀያ ሺህ ብር ሽልማት ተበርክቶላቸዋል፡፡

ፌድሬሽኑ በድምሩ ለሽልማቱ እስከ ስምንት መቶ ሺህ ብር ድረስ ወጪ ማድረጉ ታውቋል፡፡


© ሶከር ኢትዮጵያ