የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን የዳኞች ኮሚቴ አባላት ታውቀዋል

በቅርቡ የስራ አስፈፃሚ ኮሚቴ የስራ ድርሻ ሽግሽግ በማድረግ የዳኞች ኮሚቴ ዋና ሰብሳቢ አቶ ኢብራሂም አህመድ ሆኖ መሾማቸውን መዘግባችን የሚታወስ ነው።

ዐምና ኮሚቴውን ሲመሩ ከነበሩት አቶ ዮሴፍ ተስፋዬ ቦታውን ተረከቡት አቶ ኢብራሂም አህመድ ለኮሚቴው አባላትን በመምረጥ የግለሰቦቹን ፍቃደኝነት እየጠበቁ እንደሆነ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል። በዚህም መሠረት መኮንን አስረስ (ኢንስትራክተር) ለኮሚቴው ምክትል ሰብሳቢነት ሲመረጡ ኃይለመላክ ተሰማ (ኢንስትራክተር)፣ ፍቃዱ ጥላሁን (ኮሚሽነር)፣ ቸርነት አሰፋ (ኢንስትራክተር) እንዲሁም ሻለቃ በልሁ ኃይለማርያም በኮሚቴ አባልነት ለመካተት በሰብሳቢው የተመረጡ ግለሰቦች እንደሆኑ ለማወቅ ተችሏል።

በተያያዘ ዜና በኮሚቴው ሥር የሚገኘው የእግርኳስ ጨዋታ ሕጎች ቴክኒክ ፓናል ባለፈው ሳምንት ዓለም አቀፍ የእግርኳስ ቦርድ ከሰኔ 2019 ጀምሮ ተግባራዊ የሆነው የጨዋታ ሕግን አስመልክቶ ያዘጋጀውን መፅሀፍ ወደ አማረኛ በመተርጎም ለፌዴሬሽኑ አስረክቧል።


© ሶከር ኢትዮጵያ