ከፍተኛ ሊግ | ስልጤ ወራቤ ተጨማሪ ተጫዋች አስፈረመ

ከወላይታ ድቻ የታዳጊ ቡድን የተገኘው ሀብታለም ታፈሰ ስልጤ ወራቤን ተቀላቅሏል፡፡

አስቀድሞ የበርካታ አዳዲስ ተጫዋቾችን ዝውውር ከመፈፀም ባለፈ የነባሮችን ውል ሲያራዝም የነበረው የአሰልጣኝ አብዱልወኪል አብዱልፈታህ ስልጤ ወራቤ በተከላካይ አማካይ እና በአጥቂ ስፍራ ላይ መጫወት የሚችለው ወጣቱን ተጫዋች ሀብታለም ታፈሰን አስፈርሟል፡፡

በወላይታ ድቻ ከ17 እና 20 አመት በታች ቡድኖች ውስጥ በመጫወት እግር ኳስን በክለብ ደረጃ መጫወት የጀመረው ይህ ሁለገብ ተጫዋች በተጠናቀቀው የውድድር አመት በአሰልጣኝ ዘነበ ፍሰሀ አማካኝነት በወላይታ ድቻ ዋናው ቡድን አድጎ ሲጫወት የነበረ ሲሆን ዘንድሮ በክረምቱ ወደ ደቡብ ፖሊስ አምርቶ ለመጫወት ቢስማማም ክለቡን በስምምነት በመልቀቅ ማረፊያውን ስልጤ ወራቤ አድርጓል፡፡


© ሶከር ኢትዮጵያ