ከፍተኛ ሊግ | ከምባታ ሺንሺቾ አስር ተጫዋቾችን ሲያስፈርም የአሰልጣኙን ውል አራዘመ

የከፍተኛ ሊጉ ተወዳዳሪ ክለብ ከምባታ ሺንሺቾ የአሰልጣኙ አስፋው መንገሻን ውል ሲያራዝም አስር አዳዲስ ተጫዋቾችንም ማስፈረም ችሏል፡፡

ዐምና ክለቡን በዋና አሰልጣኝነት ሲመራ የነበረው አስፋው መንገሻ ለተጨማሪ ዓመት በክለቡ ለመቆየት ውሉን ያራዘመ ሲሆን አሰልጣኙም በክለቡ ለመቆየት ከተስማማ በኃላ አስር ተጨማሪ አዳዲስ ተጫዋቾችን በማስፈረም በክለቡ ውስጥ ውል በነበራቸው አስራ አምስት ተጫዋቾች ላይ ቀላቅሏል፡፡

ዘሪሁን ታፈሰ (ተከላካይ ሰሜን ሸዋ ደብረብርሃን)፣ ታረቀኝ ታደሰ (ተከላካይ ከየካ ክ/ከተማ)፣ መልካሙ ዶለና (ተከላካይ ከሰበታ ከተማ)፣ ዮርዳኖስ ዮሐንስ (ተከላካይ ከመተሀራ)፣ ወንድማገኝ በለጠ (አማካይ ከኢኮስኮ)፣ ወንድማገኝ በክር (አማካይ ከሻሸመኔ ከተማ)፣ ብሩክ ዳንኤል (አማካይ ከአቃቂ ቃሊቲ) ፍስሀ ቶማስ (አጥቂ ከኮንሶ)፣ ተመስገን ተስፋዬ (አጥቂ ከአረካ ከተማ)፣ ሀብታሙ ከበደ (አጥቂ ከየካ ክ/ከተማ) ክለቡ ያስፈረማቸው አዳዲስ ተጫዋቾች ናቸው፡፡


© ሶከር ኢትዮጵያ