ሲዳማ ቡና ለቡድኑ አባላት ሽልማት አበረከተ

በ2011ፕሪምየር ሊግ ሁለተኛ ሆኖ ያጠናቀቀው እና ዘንድሮ ደግሞ በትግራይ ዋንጫ ሻምፒዮን ለሆነው ሲዳማ ቡና ከሁለት ሚሊዮን ብር በላይ ወጪ በማድረግ ለቡድኑ አባላት ሽልማት አበረከተ፡፡

ከዐምናው ውጤታማ ጉዞ በጨማሪ ዘንድሮ በትግራይ ዋንጫ ላይ ተሳታፊ በመሆን በፍፃሜው ወላይታ ድቻን በመርታት የውድድሩ አሸናፊ የሆነው ክለቡ ውጤታማ እንዲሆን ላደረጉት የክለቡ ተጫዋቾች እና የአሰልጣኝ ቡድን አባላት ከሁለት ሚሊዮን ብር በላይ ወጪ በማድረግ ሽልማት አበርክቷል፡፡

በዚህም መሠረት በቡድኑ ውስጥ በ2011 ሲጫወቱ ለነበሩ ተጫዋቾች እና አሰልጣኞች ቡድን አባላት ለእያንዳንዳቸው መቶ ሺህ ብር እንዲሁም ዘንድሮ በትግራይ ዋንጫ ላይ ባስመዘገቡት ውጤት ደግሞ ተጨማሪ አስር ሺህ ብር ሽልማት ሸልሟል፡፡


© ሶከር ኢትዮጵያ