ቻን 2016፡ ዲ.ሪ. ኮንጎ ለፍፃሜ አለፈች 

 

በሩዋንዳ አዘጋጅነት በመካሄድ ላይ ባለው የቻን ዋንጫ አንድ የግማሽ ፍፃሜ ጨዋታ ዛሬ ተደርጎ ኮንጎ ዴሞክራቲክ ሪፐብሊክ ጊኒን በመለያ ምት 5-4 አሸንፋ ለሁለተኛ ግዜ ለፍፃሜ ደርሳለች፡፡

ጊኒ ሳይጠበቅ ናይጄሪያ እና ቱኒዚያን ከውድድር ብታስወጣም ዛሬ ለኮንጎ እጅ ሰጥታለች፡፡ ሁለቱ ብሄራዊ ቡድኖች መደበኛውን 90 ደቂቃ ያለምንም ግብ ያጠናቀቁ ሲሆን በተጨማሪው 30 ደቂቃ የቲፒ ማዜምቤው አጥቂ ጆናታን ቦሎንጊ በግምባር በመግጨት ኮንጎን መሪ አድርጓል፡፡ ኢብራሂማ ሳንኮሆን የጊኒን አቻነት ግብ ከመረብ አዋህዶ ተጨማሪው ደቂቃ 1-1ሲጠናቀቅ አሸናፊውን ለመለየት በተሰጡ የመለያ ምቶች ኮንጎ ጊኒን 5-4 በማሸነፍ የአፍሪካ ሃገራት ዋንጫን ለሁለተኛ ግዜ ለማሸነፍ ከጫፍ ደርሳለች፡፡

ነገ በሌላኛው የግማሽ ፍፃሜ ጨዋታ ኮትዲቯር ከማሊ ይጫወታሉ፡፡ አሸናፊው ኮንጎን በፍፃሜው ሲገጥም ተሸናፊው ለሶስተኛ ደረጃ ከጊኒ ጋር ይጫወታል፡፡

ኮንጎ ለፍፃሜ ሁለት ግዜ በማለፍ ከጋና ጋር የተስተካከለች ሲሆን ውድድሩን ማሸነፍ ከቻለች ደግሞ ለሁለተኛ ግዜ ማሸነፍ የቻለች ብቸኛዋ ሃገር ትሆናለች፡፡

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *