ሰበታ ከተማ አራት የውጪ ዜጋ ተጫዋቾቹን ይጠቀማል

ከፖስፖርት እና ከመኖሪያ ፍቃድ ጋር በተገናኘ በመጀመሪያው ሳምንት የፕሪምየር ሊግ ጨዋታ ሳይሰለፉ የቀሩት አራት የሰበታ ከተማ የውጪ ተጫዋቾች ቡድኑ ከቅዱስ ጊዮርጊስ ጋር በሚያደርገው ጨዋታ ወደ ሜዳ ይመለሳሉ።

የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ በመጀመሪያው ሳምንት መርሀ ግብር ሰበታ ከተማ በአዲስ አበባ ስታዲየም በወልዋሎ የ3ለ1 ሽንፈት ማስተናገዱ ይታወሳል፡፡ በዚህ ጨዋታ ላይ አራት የሰበታ ከተማ የውጪ ተጫዋቾች ማለትም ጋናዊው ግብ ጠባቂ ዳንኤል አጃይ፣ ዩጋንዳዊው ተከላካይ ሳቪዮ ካቩጉ እንዲሁም ቡሩኪና-ፋሶዋዊያኑ አጥቂዎች ሲይላ አሊ ባድራ እና ባኑ ዲያዋራ ከፓስፖርት እና የመኖሪያ ፍቃድ በጊዜው ካለማለቁ የተነሳ በጨዋታው ላይ መሰለፍ ያልቻሉ ሲሆን ዛሬ በ11:00 ሰበታ ከተማ ከ ቅዱስ ጊዮርጊስ እንደሚያደርጉት በሚጠበቀው የሁለተኛ ሳምንት ጨዋታ ሙሉ በሙሉ ጉዳያቸው በመጠናቀቁ እንደሚሰለፉ የክለቡ ሥራ-አስኪያጅ አቶ ዓለማየሁ ምንዳ ለሶከር ኢትዮጵያ ጠቁመዋል፡፡


© ሶከር ኢትዮጵያ