ኢሳይያስ ጂራ የሴካፋ ሁለተኛ ምክትል ፕሬዝዳንት ሆነው ተመረጡ

ሴካፋ ዛሬ ባካሄደው ጠቅላላ ጉባዔ ፕሬዝዳንት እና ምክትል ፕሬዝዳንቶቹን መርጧል።

የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ፕሬዝዳንት ኢሳይያስ ጅራ የተሳተፉበት የሴካፋ ፕሬዝዳንትነት ምርጫ ዛሬ ሲጠናቀቅ ታንዛንያዊ ዋላሴ ካርያ ሴካፋን በፕሬዝዳንትነት እንዲመሩ ተመርጠዋል። ደቡብ ሱዳናዊው ፍራንሲስ አሚን ተቀዳሚ ምክትል ፕሬዝዳንት ሆነው እንዲመሩ የተመረጡ ሲሆን ኢሳይያስ ጂራ ሁለተኛ ምክትል ፕሬዝዳንት እንዲሆኑ ተመርጠዋል።

አስራ ሁለት አባል ሃገራት የያዘውና መቀመጫውን በኬንያ አድርጎ በ1926 የተመሰረተው አንጋፋው ማኅበር ከዚህ በፊት ለ20 ዓመታት በኒኮላስ ሙሶንዬ ዋና ፀሐፊነት ሲመራ መቆየቱ ሲታወስ ካፍ ባስቀመጠው አዲስ መመርያ መሠረት አወቃቀሩን ቀይሮ በፕሬዝዳንት፣ ም/ፕሬዝዳንት እና ሥራ አስፈፃሚ ኮሚቴ አባላት የሚመራው የክፍለ አህጉሩ ማኅበር ለቀጣዮቹ ዓመታት በታንዛንያ እግርኳስ ፌዴሬሽን ፕሬዝዳንት ዋላሴ ካርያ የሚመራ ይሆናል።


© ሶከር ኢትዮጵያ