የዲሲፕሊን ኮሚቴ ሦስት ስሐል ሽረ ቡድን አባላትን ለማነጋገር ቀጠሮ ይዟል

የስሑል ሽረ የቡድን አባላት የሆኑት ሦስት ግለሰቦችን የዲሲፕሊን ኮሚቴ ጠርቶ ለማነጋገር ለነገ (ሰኞ) ቀጠሮ ይዟል።

ስሑል ሽረ ባሳለፍነው ሳምንት በሊጉ አራተኛ ሳምንት በአዲስ አበባ ስታዲየም ከቅዱስ ጊዮርጊስ ጋር ያደረገው ጨዋታ ያለ ጎል በአቻ ውጤት መጠናቀቁ ይታወቃል።

የፌዴሬሽኑ የዲሲፕሊን ኮሚቴም በዚህ ጨዋታ ላይ ያልተገባ ባህሪ አሳይተዋል በማለት ሦስት የስሑል ሽረ የቡድን አባላትን ለማናገር ጥሪ ነው ያደረገው። እነርሱም ምዑዝ ኃይለሚካኤል (የግብ ጠባቂዎች አሰልጣኝ)፣ መብራህቶም ፍስሀ (ም/አሰልጣኝ) እና በረከት ገብረመድህን (ቴክኒክ ዳሬክተር) ናቸው ነገ 09:00 በአዲስ አበባ ስታድየም በሚገኘው ቢሮ እንዲገኙ ኮሚቴው ጥሪ ያደረገላቸው።

ከዲሲፕሊን ኮሚቴው ጋር ተያይዞ የፋሲል ከነማው አሰልጣኝ ሥዩም ከበደም በሆሳዕና ሜዳ ዙርያ ባሰፈሩት አስተያየት ላይ ማብራርያ እንዲሰጡ ለነገ ቀጠሮ መያዙ የሚታወስ ነው።


© ሶከር ኢትዮጵያ