የኢትዮጵያ ሴቶች ብሄራዊ ቡድን የካቲት 27 ከአልጄርያ ጋር ለሚያደርገው የ2016 የአፍሪካ ሴቶች ዋንጫ ማጣርያ በመጪው የካቲት 10 ዝግጅት ይጀምራል፡፡ የብሄራዊ ቡድኑ አሰልጣን ሆነው የተመረጡት አሰልጣኝ ብርሃኑ ግዛው ለዝግጅታቸው 30 ተጫዋቾችን የጠሩ ሲሆን የአምናው የፕሪሚየር ሊግ እና የአሸናፊዎች አሸናፊ ዋንጫ ቻምፒዮን የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ 11 ተጫዋቾችን አስመርጧል፡፡ ከ17 አመት በታች ቡድን አባል የነበረችው ትደግ ፍስሃ ፣ ከ20 አመት በታች ብሄራዊ ቡድን ውስጥ የነበሩት ታሪኳ በርገና ፣ አሳቤ ሙሶ ፣ ሀብታም እሸቱ ፣ ሎዛ አበራ ፣ ሔለን እሸቱ እና መዲና አወል እንዲሁም በብሄራዊ ቡድን ልምድ ያላቸው ዳግማዊት መኮንን ፣ ይወት ደንጊሶ ፣ ረሒማ ዘርጋ እና ሽታዬ ሲሳይ በዋናው ብሄራዊ ቡድን ተካተዋል፡፡
በአሰልጣኝ ብርሃኑ ግዛው የተመረጡት 30 ተጫዋቾች የሚከተሉት ናቸው፡-
ግብ ጠባቂዎች
ዳግማዊት መኮንን – የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ
ንግስት መዓዛ – የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ
ፍሬወይኒ ገ/መስቀል – ደደቢት
ታሪኳ በርገና – ድሬዳዋ ከተማ
ተከላካዮች
ውባለም ፀጋዬ – ደደቢት
መስከረም ኮንካ – ደደቢት
አሳቤ ሞሶ – ዳሽን ቢራ
ፋሲካ በቀለ – ዳሽን ቢራ
ፅዮን እስጢፋኖስ- የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ
ጥሩነሽ መንገሻ – የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ
እፀገነት ብዙነህ – የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ
ሀብታም እሸቱ – የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ
ገነት ፍርዴ – አዳማ ከተማ
አማካይ
ህይወት ደንጊሶ – የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ
ቅድስት ቦጋለ – የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ
ብሩክታዊት ግርማ – የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ
ብርቱካን ገ/ክርስቶስ- ደደቢት
ኤደን ሽፈራው – ደደቢት
እመቤት አዲሱ – መከላከያ
አዲስ ንጉሴ – ሀዋሳ ከተማ
የካቲት መንግስቱ – ሲዳማ ቡና
ፅዮን ፈየራ – ኤሌክትሪክ
አጥቂዎች
ሽታዬ ሲሳይ – የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ
ረሒማ ዘርጋ – የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ
ሎዛ አበራ – ደደቢት
መዲና አወል – ቅድስተ ማሪያም
ትዕግስት ዘውዴ – ቅዱስ ጊዮርጊስ
ሔለን እሸቱ – ዳሽን ቢራ
ትደግ ፍስሃ – ጥሩነሽ ዲባባ አካዳሚ
ሰርካዲስ ጉታ – ዳሽን ቢራ