ምስር አል ማቃሳ እና ሴንት ሚሼል ልምምዳቸውን በአአ ስታድየም አድርገዋል

 

የሀገራችንን ሁለት ክለቦች በአፍሪካ ኮንፌደሬሽን ዋንጫ እንዲሁም በአፍሪካ ቻምፒዬንስ ሊግ ለመግጠም አዲስ አበባ የገቡት የግብፅ እና የሲሸልስ ክለቦች ዛሬ በአዲስ አበባ ስታዲየም ልምምዳቸውን አድርገዋል፡፡

ከትላንት በስቲያ አዲስ አበባ የደረሱት ምስር አል ማቅሳዎች ከጨዋታው ከ24 ሰዓት በፊት በሚጫወቱበት አዲስ አበባ ስታዲየም ልምምዳቸውን ዛሬ ከ10፡25 ጀምሮ አከናውነዋል፡፡ 25 ያክል ደቂቃዎችን በፈጀው የልምምድ ጊዜያቸው ቀለል ያሉ ልምምዶችን ሲያደርጉ ቡድኑ እንደሌሎቹ የአፍሪካ ክለቦች የመስመር ኳሶች ላይ መሰለት ያደረገ ልምምድ ሲያደርጉ አልታዩም፡፡

አብዛኛውን የልምምድ ጊዜያቸውን በአጭር ሜዳ ላይ ለሁለት ተከፍሎ በመጫወት እና ሰውነት የማሳሳብ ስራ በመስራት አሳልፈዋል፡፡

ከነገ በስቲያ የሊግ ቻምፒዮኑ ቅዱስ ጊዮርጊስን የሚገጥመው የሲሸልሱ ሴይንት ሚሼል በተመሳሳይ ዛሬ በአዲስ አበባ ስታዲየም ከምስር አል ማቃሳ ቀጥሎ ረዘም ያለ ጊዜ የረጀ ልምምድ አድርጎዋል፡፡

65 ደቂቃ የፈጀው የሴይንት ሚሼል ልምምድ ተጨዋቾቹ የአዲስ አበባን የአየር ፀባይ እንዲለምዱት በሚመስል መልኩ አብዛኛውን ጊዜ የወሰዱት ሜዳውን በፍጥነት እንዲሁም በዝግታ መሮጥ ነው፡፡ ከልምምዳቸው እንደተረዳነው ቡድኑ አጫጭር ኳሶችን መጠቀም እና ፍጥነት ያላቸው ተጫዋቾች ላይ መሰረት ያደረገ የአጨዋወት ስልት ላይ የሚያተኩር ይመስላል፡፡

ሀገራችንን በክለብ ደረጃ በኢንተርናሽንል መድረክ የሚወክሉት ሁለቱ ክለቦች ነገና ከነገ በስቲያ በአዲስ አበባ ስታዲየም ጨዋታቸውን የሚያደርጉ ይሆናል፡፡

image-b6ce92b0322be9ee673b98e424d5b38b4dcfaf1fc5f5739bccba1d40edaaf4ff-V

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *