ቅዱስ ጊዮርጊስ በአዲስ ማልያ ሴንት ሚሼልን ይገጥማል

 

የቅዱስ ጊዮርጊስ ስፖርት ማህበር በአለም አቀፉ የትጥቅ አምራች ኩባንያ ማክሮን የተዘጋጀውን 16 አይነት የተጨዋቾች መገልገያ እቃዎች በዛሬው እለት ለተጨዋቾች አከፋፈለ፡፡

ባሳለፍነው ሳምንት ክለቡ ባሳወቀው መረጃ ተጨዋቾች በጨዋታ ወቅት ይለብሱዋቸው የነበሩት ማልያ እና መጋጫ ብቻ ሀገራችን ገብተው የነበረ ሲሆን አዲስ አበባ የሚገኘው የማክሮን ወኪል በትናንትናው ዕለት ሁሉም እቃዎችን በማስገባቱና ለስፖርት ማህበሩ በማስረከቡ ዛሬ ለሁሉም ተጨዋቾች ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን በማክሮን አርማ የተሰሩ እቃዎችን አከፋፍሏል፡፡

1. ሾርት ቁምጣ 2. ሎቶ ፖሎ ቲሸርት 3. ነጭ ፓካውት 4. ሎሚማ የምግብ ቤት ቲሸርት 5. ቀይ ቦዲ 6. ነጭ ካልሲ 7. ነጠላ ጫማ 8. የጫማ መያዣ ቦርሳ 9. ቀይ ታይት 10. ኦሬንጅ ታይት 11. ቀይ ኮፍያ 12. ፎጣ 13. ሎቶ ስኒከር 14. ቢጫ ቱታ ከነ ቲሸርቱ 15. መጋጫ 16. የትጥቅ መያዣ ቦርሳ

የቅዱስ ጊዮርጊስ ተጨዋቾች እና መላው የቡድኑ አባላት እነዚህን እቃዎች ከዛሬ ጀምሮ የሚጠቀሙባቸው ሲሆን በአዲስ መልክ የተሰራው ማልያም ቅዱስ ጊዮርጊስ በመጪው እሁድ በአፍሪካ ቻምፒየንስ ሊግ ከሴንት ሚሼልስ ቡድን ጋር ሲጫወት የሚለብሱት ይሆናል፡፡

 

(ዜናው የተላከው ከቅዱስ ጊዮርጊስ ስፖርት ማህበር ህዝብ ግንኙነት ነው)

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *