አዳማዎች በድጋሚ ልምምድ መስራት አቁመዋል

ዋና አሰልጣኙ አሸናፊ በቀለን ጨምሮ የአዳማ ተጫዋቾች መደበኛ ልምምዳቸውን አቋርጠዋል።

ከመጥፎው የውጤት ጉዞ አገግመው በጥሩ ወቅታዊ አቋም ላይ የሚገኙት አዳማዎች ባለፈው ሳምንት ኢትዮጵያ ቡናን 3-0 በማሸነፍ ደረጃቸውን ማሻሻል ቢችሉም አሁንም የቡድኑ ውስጣዊ ችግር አለመፈታት በቀጣይ ጉዟው ላይ ዳግም እንቅፋት እንዲፈጥርባቸው አድርጓል። የደሞዝ ጥያቄው አለመፈታቱን ተከትሎም የቡድኑ አባላት ልምምዳቸውን ካቋሙ ሁለት ቀን የሆናቸው ሲሆን ሲሆን በቀጣይ ሰኞ ከሲዳማ ቡና ጋር ለሚያደርጉት ጨዋታ ወደ ሀዋሳ የመጓዛቸው ጉዳይ በውል አለየለትም። አሰልጣኝ አሸናፊም ሥራቸውን ያቆሙ ሲሆን ችግሩ በቶሎ የማይቀረፍ ከሆነ በርካታ ተጫዋቾች ከቡድኑ ሊለቁ እንደሚችሉ ሰምተናል።

ሰለቡድኑ እና በክለቡ ያሉ አዳዲስ ነገሮችን እየተከታተልን እናቀርባለን።

© ሶከር ኢትዮጵያ