ደደቢት በዲሲፕሊን ኮሚቴ እገዳ ተላለፈበት

በከፍተኛ ሊግ እየተወዳደሩ የሚገኙት ደደቢቶች ባለፉት 8 ዓመታት ቡድኑት ካገለገለው የመስመር ተጫዋቹ ብርሀኑ ቦጋለ ጋር በተያያዘ ጉዳይ የእግድ ውሳኔ ተላልፎባቸዋል።

ተጫዋቹ ባቀረበው አቤቱታ መሰረት የፍትህ አካላት የወሰኑት ውሳኔ ተግባራዊ እንዲያደርጉ ደደቢቶች ተወስኖባቸው የነበረ ቢሆንም ያላቸውን ችግር ጠቅሰው ተጨማሪ ጊዜ እንዲሰጣቸው በጠየቁት መሰረት የፍትህ አካሉ እስከ ጥር 08 ቀን 2012 ውሳኔውን ተግባራዊ እንዲያደርጉ ቢወሰንባቸውም በተሰጣቸው የግዜ ገደብ ውሳኔውን ተግባራዊ ባለማድረጋቸው ተፈፃሚ እስከሚያደርጉ ድረስ ከማንኛውም አገልግሎት መታገዳቸውን ጉዳዩን ከያዙት የህግ ባለሙያ አቶ ብርሀኑ በጋሻው ማረጋገጥ ችለናል።

© ሶከር ኢትዮጵያ