አክሊሉ ዋለልኝ ወደ ወልዋሎ ተጉዟል

የአማካይ ስፍራ ተጫዋቹ አክሊሉ ዋለልኝ ወልዋሎን በይፋ ተቀላቀለ፡፡

ከሀዋሳ ከተማ ታዳጊ ቡድን ከተገኘ በኋላ በዋናው ቡድን በመጫወት የክለብ ህይወትን የጀመረው ይህ አማካይ ከሀዋሳ ከተማ በመቀጠል በኢትዮጵያ ቡና እና ጅማ አባ ጅፋር በመጫወት አሳልፏል፡፡ በያዝነው ዓመት መስከረም ወር ላይ አባ ጅፋርን በመልቀቅ ለስሑል ሽረ ፊርማውን ያኖረ ቢሆንም በክለቡ የስድስት ወራት ቀሪ ኮንትራት እየቀረው በመለያየት ማረፊያውን ወደ ወልዋሎ ፊርማውን አኑሯል፡፡

© ሶከር ኢትዮጵያ