ሦስት ተጫዋቾች ለኮሮና ቫይረስ መከላከያ የሚሆን ድጋፍ አድርገዋል

በደደቢት ፣ ስሑል ሽረ እና ሀዲያ ሆሳዕና የሚጫወቱ ሥስት ወጣት ተጫዋቾች ለኮሮና ቫይረስ መከላከያ የሚሆን የገንዘብ ድጋፍ አድርገዋል።

ከዚህ ቀደም በርካታ ክለቦች ፣ ተጫዋቾች እና የደጋፊ ማሕበራት ለወረርሺኙ መከላከያ የሚሆን የገንዘብ እና የቁሳቁስ ድጋፎች ማድረጋቸው የሚታወስ ሲሆን አሁን ደግሞ ከክለቡ ጋር ድንቅ ዓመት እያሳለፈ የሚገኘው የስሑል ሽረው ነፃነት ገብረመድኅን፣ በቅርቡ ወደ ሀዲያ ሆሳዕና ያመራው መድሀኔ ብርኃኔ እና የሰማያዊዎቹን የማጥቃት ክፍል የመራውና በአሁኑ ሰዓት ቀዶ ጥገና አድርጎ በጥሩ ጤንነት ላይ የሚገኘው ከድር ሳልህ ለወረርሺኙ መከላከያ ድጋፍ አድርገዋል።

👉እጅዎን በተደጋጋሚ በሳሙና በአግባቡ በመታጠብ አልያም አልኮል እና ሳኒታይዘር በመጠቀም

👉ከሰዎች ጋር ንክኪ በማስወገድ

👉ከአላስፈላጊ እንቅስቃሴ በመገደብ፣ አካላዊ ርቀት በመጠበቅ እና በቤት በመቆየት ራሳችንን ከኮሮና ቫይረስ እንጠብቅ!


© ሶከር ኢትዮጵያ