ወንድማማች ተጫዋቾች ለአረጋውያን ድጋፍ አደረጉ

ዳንኤል እና መሐሪ አድሐኖም ለአቅመ ደካማ አረጋውያን ድጋፍ አድርገዋል፡፡

የኮሮና ቫይረስን ለመግታት እና ለቅድመ ጥንቃቄ ይረዳ ዘንድ በርካቶች በቁሳቁስ እና በገንዘብ ድጋፋቸውን ማድረግ ቀጥለዋል፡፡ በስፖርቱ ዘርፍ የተሰማሩ የተለያዩ አካላትም እየተረባረቡ ሲሆን በአሁኑ ሰዓት ለደደቢት እየተጫወተ የሚገኘው የመስመር ተከላካዩ ዳንኤል አድሐኖም እና ለከፍተኛ ሊጉ ሶሎዳ ዓድዋ እየተጫወተ የሚገኘው ወንድሙ መሐሪ አድሐኖም በዓድዋ ከተማ ለሚገኙና ከቤታቸው መውጣት ለማይችሉ አቅመ ደካማ አረጋዊያን ገንዘብ በማውጣት ቁሳቁሶች እና ምግቦችን ዛሬ ከሰዓት ለግሰዋል፡፡

👉እጅዎን በተደጋጋሚ በሳሙና በአግባቡ በመታጠብ አልያም አልኮል እና ሳኒታይዘር በመጠቀም

👉ከሰዎች ጋር ንክኪ በማስወገድ

👉ከአላስፈላጊ እንቅስቃሴ በመገደብ፣ አካላዊ ርቀት በመጠበቅ እና በቤት በመቆየት ራሳችንን ከኮሮና ቫይረስ እንጠብቅ!


© ሶከር ኢትዮጵያ