ሲዳማ ቡና ለኮሮና ቫይረስ መከላከያ ድጋፍ አደረገ

የሲዳማ ቡና ተጫዋቾች፣ አሰልጣኞች እና አጠቃላይ የክለቡ ሠራተኞች ለኮሮና ቫይረስ መከላከያ የሚውል የገንዘብ ድጋፍን አድርገዋል፡፡

የኮሮና ቫይረስ ስርጭትን ለመግታት በርካቶች በገንዘብ እና በአይነት እየገለሱ ሲሆን በርካታ ተከታይ ያለው የስፖርቱ ዘርፍም ለዚህ ቅድመ መከላከል የራሱን እገዛ እያበረከተ ይገኛል፡፡ አሁን ደግሞ የሲዳማ ቡና አሰልጣኞች እና ተጫዋቾች እንዲሁም በክለቡ ስር ያሉ ሁሉም ሰራተኞች ለዚህ በጎ አላማ እንዲውል ከአንድ ወር ደመወዛቸው ግማሹን አበርክተዋል፡፡ ከዚህም ባሻገር በተለያዩ በጎ ተግባራት ላይ የክለቡ ደጋፊዎች አስተዋጽኦ እያደረጉ ሲሆን ይህንንም ድጋፍ ክለቡ በተጠናከረ መልኩ እንደሚያስቀጥል የክለቡ ሥራ አስኪያጅ አቶ መንግስቱ ሳሳሞ ለሶከር ኢትዮጵያ ተናግረዋል፡፡

👉እጅዎን በተደጋጋሚ በሳሙና በአግባቡ በመታጠብ አልያም አልኮል እና ሳኒታይዘር በመጠቀም

👉ከሰዎች ጋር ንክኪ በማስወገድ

👉ከአላስፈላጊ እንቅስቃሴ በመገደብ፣ አካላዊ ርቀት በመጠበቅ እና በቤት በመቆየት ራሳችንን ከኮሮና ቫይረስ እንጠብቅ!


© ሶከር ኢትዮጵያ