የድሬዳዋ ከተማ የሴት ቡድን አባላት ለኮሮና ቫይረስ መከላከያ የሚውል ድጋፍ አደረጉ

የድሬዳዋ ከተማ የሴት ቡድን አባላት ለወረርሺኙ መከላከያ ከአንድ ወር ደሞዛቸው ግማሹን ለግሰዋል።

ድሬዳዋ ከተማዎች በሀገር አቀፍ ደረጃ የኮሮና ቫይረስ ወረርሺኝን ለመከላከል የተጀመረውን እንቅስቃሴ በመደገፍ ከፍተኛ እንቅስቃሴ በማድረግ ላይ ከሚገኙ ቡድኖች አንዱ ሲሆን ትናንት የወንዶች ቡድን የአንድ ወር ደሞዛቸውን ለዚህ ዓላማ ማበርከታቸው ይታወሳል። አሁን ደግሞ የሴቶች ቡድን አባላት የግማሽ ወር ደሞዛቸውን ለግሰው ከሴት ቡድኖች የመጀመሪያ በመሆን እንቅስቃሴውን ተቀላቅለዋል። በተጓዳኝም የክለቡ የቦክስ እና ብስክሌት ቡድንም ድጋፍ ማድረጋቸው ታውቋል።

👉እጅዎን በተደጋጋሚ በሳሙና በአግባቡ በመታጠብ አልያም አልኮል እና ሳኒታይዘር በመጠቀም

👉ከሰዎች ጋር ንክኪ በማስወገድ

👉ከአላስፈላጊ እንቅስቃሴ በመገደብ፣ አካላዊ ርቀት በመጠበቅ እና በቤት በመቆየት ራሳችንን ከኮሮና ቫይረስ እንጠብቅ!


© ሶከር ኢትዮጵያ