ቅዱስ ጊዮርጊስ ጊዜያዊ አሰልጣኝ ሾመ

ፈረሰኞቹ ከሀያ ዓመት በታች ቡድን ዋና አሰልጣኝ የሆነው ደረጀ ተስፋዬ (አንገቴ) ጊዜያዊ ዋና አሰልጣኝ አድርጓል፡፡

ከቀናት በፊት የቅዱስ ጊዮርጊስ የቦርድ አመራር የክለቡን ዋና አሰልጣኝ ሰርዳን ዝቦጅኖቭን ጨምሮ ረዳት አሰልጣኙን ዘሪሁን ሸንገታን ሲያግድ የግብ ጠባቂውን አሰልጣኝ ጋንዳ ኤሚን በማሰናበት እንዲሁም ሌሎች ተጨማሪ ውሳኔዎችን መወሰኑ ይታወሳል፡፡ ክለቡ ከሰበታ ከተማ በነበረው ጨዋታም ካለ ዋና አሰልጣኝ ወደ ሜዳ የገባ ሲሆን በውጤቱም 1ለ0 ሽንፈት ማስተናገዱም ይታወሳል፡፡

ክለቡም ለቀጣዮቹ የሊጉ ጨዋታዎች ዋና አሰልጣኝ እስከሚያገኝ ድረስ ጊዜያዊ አሰልጣኝ በማድረግ ደረጀ ተስፋዬ ሾሟል፡፡ አሰልጣኙ ለረጅም ዓመታት የቅዱስ ጊዮርጊስ ከ17 ዓመት በታች ዋና አሰልጣኝ በመሆን የሰራ ሲሆን ከ2011 ጀምሮ ደግሞ ከሀያ ዓመት በታች ቡድኑን እያሰለጠ ይገኛል። በኢትዮጵያ ከ17 ዓመት በታች ቡድንም የተመስገን ዳና ረዳት ሆኖ ሰርቷል። 

አሰልጣኝ ደረጄ ከዛሬ ጀምሮ ቡድን በመረከብ ወደ ዝግጀት እንደሚገባ ሶከር ኢትዮጵያ ያገኘችው መረጃ ይጠቁማል፡፡

© ሶከር ኢትዮጵያ