በተለያዩ ክለቦች የሚገኙ ተጫዋቾች ድጋፍ ማድረጋቸው ቀጥለዋል

በጌዴኦ ዲላ፣ ስሑል ሽረ፣ መቐለ፣ ወልዋሎ እና ደደቢት የሚጫወቱ ተጫዋቾች ለኮሮና ቫይረስ መከላከያ የሚውል የገንዘብ ድጋፍ አድርገዋል።

በዛሬው ዕለት ድጋፍ አድርገው እንቅስቃሴውን የተቀላቀሉት የጌዴኦ ዲላው ወልዳይ ገብረሥላሴ፣ የወልዋሎው ያሬድ ብርሀኑ፣ የመቐለው ምሕረትአብ ገብረህይወት፣ የስሑል ሽረዎቹ ሸዊት ዮሐንስ እና ብሩክ ሐድሽ፣ የደደቢቶቹ ክብሮም አስመላሽ እና ዳዊት ዑቁበዝጊ ናቸው።

ከዚህ ቀደም በተጠቀሱት ክለቦች የሚገኙ አስራ ሁለት ተጫዋቾች በጋራ ለወረርሺኙ መከላከያ የሚውል ድጋፍ ማድረጋቸው የሚታወስ ሲሆን በቀጣይ ቀናትም ሌሎች ተጨማሪ ተጫዋቾች ድጋፍ ለማድረግ በዝግጅት እንደሚገኙ ለማወቅ ተችሏል።

እስካሁን ቅዱስ ጊዮርጊስ ከአጋር ድርጅቶቹ ጋር ፣ የዳኞች እና ታዛቢዎች ሙያ ማሕበር፣ የወልቂጤ ከተማ ምክትል ፕሬዝዳንት አቶ አበባው ሰለሞን፣ የአዲስ አበባ እግርኳሰ ፌዴሬሽን እና ካርሎስ ዳምጠውን ጨምሮ በርከት ያሉ ተጫዋቾች በጋራ ለወረርሺኙ መከላከያ ድጋፍ ማድረጋቸው ይታወሳል።

© ሶከር ኢትዮጵያ