ጅማ አባጅፋር የላኪ ሰኒንን ዝውውር አጠናቋል

በሙከራ አስር ቀናትን በጅማ አባጅፋር ያሳለፈው ናይጄሪያዊው አጥቂ ላኪ ሰኒ ከዝውውር መዘጋቱ ቀደም ብሎ ለአንድ ዓመት ፊርማውን አኑሯል፡፡

ዘጠኝ አመታትን በኢትዮጵያ ተጫውቶ ያሳለፈው ይህ የአጥቂ ስፍራ ተጫዋች በወልቂጤ ከተማ፣ ጅማ አባ ቡና፣ ሲዳማ ቡና፣ አርባምንጭ እና ደቡብ ፖሊስ በመጫወት ያሳለፈ ሲሆን ያለፈውን ስድስት ወር ያለምንም ጨዋታ በደቡብ ፓሊስ የከፍተኛ ሊግ ቡድን ውስጥ ቆይታን ካደረገ በኋላ ከክለቡ በመሰናበቱ ለአስር ቀናት ወደ ጅማ አምርቶ የሙከራ ጊዜን ካሳለፈ በኃላ በስተመጨረሻም ዝውውሩ ከመጠናቀቁ ቀደም ብሎ በይፋ ለክለቡ የአንድ ዓመት ፊርማውን አኑሯል፡፡

ጅማ አባጅፋር ከላኪ ሰኒ በተጨማሪ ከቀናት በፊት የሙከራ ዕድል የሰጡትን ወጣቱን የመስመር አጥቂ ኢብራሂም አብዱልቃድርን ማስፈረሙ ይታወሳል፡፡

© ሶከር ኢትዮጵያ