የዳኞች እና ታዛቢዎች ሙያ ማኅበር ለኮሮና ቫይረስ መከላከያ እንዲውል የገንዘብ ድጋፍ አደረገ

የኢትዮጵያ ዳኞች እና ታዛቢዎች ሙያ ማኅበር ለኮሮና ቫይረስ መከላከያ እንዲውል ለጤና ሚኒስቴር የሀምሳ ሺህ ብር የገንዘብ ድጋፍን አበርክቷል፡፡

በአለም አቀፍ ደረጃ ስጋት እየሆነ ለብዙዎች ህይወት ማለፍም ጭምር አደጋ እየሆነ የመጣው የኮሮና ኮቪዲ 19 ቫይረስ ሀገራችንም ከገባ ሰንበትበት ብሏል፡፡ ይህን አስከፊ በሽታን ለመከላከል በስፖርቱ ዘርፉ ያሉ ግለሰቦች ድርጅቶች እና ተቋማት ድጋፋቸውን እያደረጉ ሲሆን የኢትዮጵያ ዳኞች እና ታዛቢዎች ሙያ ማኅበርም ለዚህ በሽታ መከላከያ እንዲውል የሀምሳ ሺህ ብር የገንዘብ ድጋፍ ለጤና ሚኒስቴር ማበርከቱን የማኅበሩ ፕሬዝዳንት ኢንተርናሽናል ረዳት ዳኛ ትግል ግዛው ለሶከር ኢትዮጵያ ተናግሯል፡፡

© ሶከር ኢትዮጵያ