መከላከያ የገንዘብ ድጋፍ አደረገ

በዓለማችን ብሎም በሀገራችን በፍጥነት እየተስፋፋ የመጣውን የኮሮና ቫይረስ ስርጭት ለመከላከል እና ለመቆጣጠር ለሚደረገው ርብርብ የመከላከያ እግርኳስ ክለብ የገንዘብ ድጋፍ አድርጓል።

የአዋቂ የወንዶች፣ ሴቶች ቡድን እና የአሰልጣኝ አባላት በጋራ በመሆን 210 ሺህ ብር ለአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የኮሮና ቫይረስ ድጋፍ አሰባሳቢ ኮሚቴ በዛሬው ዕለት ያስረከቡት። ይህ ድጋፍ በሲቪል እግርኳስ ቡድኑ ይደረግ እንጂ በቀጣይ ቀናት የወታደር እግርኳስ ቡድን መሰል የገንዘብ ድጋፍ ሊያደርግ እንደሚችል ሰምተናል።

ወረርሽኙን ተከትሎ የሚመጡ ማኀበራዊ ችግሮችን አስቀድሞ መከላከል ይቻል ዘንድ በስፖርቱ ዘርፍ በሁሉም አቅጣጫ የሚደረገው እርብርብ በቀጠለበት በአሁኑ ሰዓት በቀጣይም መሰል ትብብሮች ተጠናክረው ሊቀጥሉ እንደሚችሉ መረጃዎች እየጠቆሙ ይገኛል።

👉እጅዎን በተደጋጋሚ በሳሙና በአግባቡ በመታጠብ አልያም አልኮል እና ሳኒታይዘር በመጠቀም

👉ከሰዎች ጋር ንክኪ በማስወገድ

👉ከአላስፈላጊ እንቅስቃሴ በመገደብ፣ አካላዊ ርቀት በመጠበቅ እና በቤት በመቆየት ራሳችንን ከኮሮና ቫይረስ እንጠብቅ!


© ሶከር ኢትዮጵያ