ኢትዮጵያዊው አጥቂ ፍቅሩ ተፈራ ወደ ባንግላዴሹ ክለብ ሼክ ሩሰል ቺካታራ የሚያደርገውን ዝውውር ለማጠናቀቅ ዳሃካ እንደሚገኝ ተነግሯል፡፡
ከቀናት በፊት ወደ ባንግላዴሽ መዲና ዳሃካ ያቀናው የቀድሞ የአዳማ ከተማ እና ቅዱስ ጊዮርጊስ ተጫዋች ፍቅሩ ወደ ሼክ ሩሰል ቺካታራ የሚያደርገው ዝውውር ግን ገና አልተጠናቀቀም፡፡ በዝውውር እና በአንዳንድ የጥቅማጥቅም ጉዳዮች ላይ ከባንግላዴሹ ክለብ ጋር እየተደራደረ የሚገኘው ተጫዋቹ በቅርብ ቀናት ዝውውሩ አልቆ ለክለቡ ለመጫወት ፊርማውን ያኖራል ተብሎ ይጠበቃል፡፡
የህንድ ሄሮ ሱፐር ሊግ ሻምፒዮን የሆነውን ቼኔይን ከለቀቀ በኃላ ክለብ አልባ ሆኖ የቆየው ፍቅሩ ከሁለት ሳምንት በፊት ወደ ባንግላዴሽ ሊግ ለማምራት ከጫፍ መድረሱ መዘገባችን የሚታወስ ነው፡፡
ፍቅሩ ባለፉት 10 ዓመታት ከኢትዮጵያ ውጪ የእግርኳስ ህይወቱን ያሳለፈ ሲሆን በስድስት ሃገራት በሚገኙ ክለቦች ተዘዋውሮ መጫወት ችሏል፡፡