ቅዱስ ጊዮርጊስ የጋናዊው ተከላካዩን ውል አራዘመ

ቅዱስ ጊዮርጊስ የጋናዊ የተከላካይ መስመር ተጫዋች ኤድዊን ፍሪምፖንግ ውል ማራዘሙን ይፋ አድርጓል።

በ2010 ክረምት ቅዱስ ጊዮርጊስን የተቀላቀለው ፍሪምፖንግ በፈረሰኞቹ የኋላ ክፍል መደበኛ ተሰላፊ መሆን የቻለ ሲሆን በተለይ በዘንድሮው የውድድር ዓመት ምርጥ አቋማቸውን ካሳዩ ተከላካዮች ግንባር ቀደሙ ነበር። ይህን ተከትሎም ለተጨማሪ ሁለት ዓመታት በክለቡ ለመቆየት መስማማቱን ክለቡ አሳውቋል።

👉እጅዎን በተደጋጋሚ በሳሙና በአግባቡ በመታጠብ አልያም አልኮል እና ሳኒታይዘር በመጠቀም

👉ከሰዎች ጋር ንክኪ በማስወገድ

👉ከአላስፈላጊ እንቅስቃሴ በመገደብ፣ አካላዊ ርቀት በመጠበቅ እና በቤት በመቆየት ራሳችንን ከኮሮና ቫይረስ እንጠብቅ!


© ሶከር ኢትዮጵያ