ድሬዳዋ ከተማ የአሰልጣኞቹን ውል አራዘመ

ድሬዳዋ ከተማ የዋና አሰልጣኙ ፍስሐ ጥዑመልሳን እና ምክትሉ እዮብ ተዋበን ኮንትራት ማራዘመኑን በፌስቡክ ገፁ አስታውቋል።

የቀደሞው የድሬዳዋ ሴቶች ቡድን አሰልጣኝ እና ከ2010 ጀምሮ የወንዶች ቡድን ምክትል አሰልጣኝ በመሆን ሲሰሩ የቆዩት ፍስሐ ጥዑመልሳን የዘንድሮው ውድድር ከተጀመረ ሳምንታት በኋላ ስምኦን ዓባይን በመተካት ዋና አሰልጣኝ ሆነው ሲሰሩ የቆዩ ሲሆን ለቀጣይ አንድ ዓመት ውላቸው መራዘሙን ክለቡ ገልጿል።

በተመሳሳይ የተስፋ ቡድኑን ሲያሰለጥን ቆይቶ ዘንድሮ የዋናው ቡድን ምክትል አሰልጣኝ የሆነው እዮብ ተዋበ ለተጨማሪ አንድ ዓመት በክለቡ ለመቆየት ተስማምቷል።

👉እጅዎን በተደጋጋሚ በሳሙና በአግባቡ በመታጠብ አልያም አልኮል እና ሳኒታይዘር በመጠቀም

👉ከሰዎች ጋር ንክኪ በማስወገድ

👉ከአላስፈላጊ እንቅስቃሴ በመገደብ፣ አካላዊ ርቀት በመጠበቅ እና በቤት በመቆየት ራሳችንን ከኮሮና ቫይረስ እንጠብቅ!


© ሶከር ኢትዮጵያ