ሲዳማ ቡና የአራት ተጫዋቾችን ውል ለማራዘም ተስማምቷል

ከሰሞኑ የአሰልጣኞቹን ውል ያደሰው ሲዳማ ቡና የአራት ወሳኝ ተጫዋቾቹን ውል ለተጨማሪ ዓመት ለማራዘም ከስምምነት ደርሷል፡፡

የቀድሞው የደቡብ ፖሊስ እና አርባምንጭ ከተማ ግብ ጠባቂ የነበረው እና ባለፉት ሦስት አመታት ደግሞ በሲዳማ ቡና ቋሚ ግብ ጠባቂ በመሆን ሲያገለግል የነበረው መሳይ አያኖ እንዲሁም የቀድሞው የደቡብ ፓሊስ ግብ ጠባቂ የሆነው እና ያለፉትን አራት ዓመታት ሲዳማ ቡናን ያገለገለው ሌላኛው ግብ ጠባቂ ፍቅሩ ወዴሳ ውላቸውን ለተጨማሪ ዓመት ለማራዘም ተስማምተዋል፡፡

ሌላኛው የክለቡ ሁለተኛ አምበል እንዲሁም በተከላካይነት እና በተከላካይ አማካኝነት በሲዳማ ቡና ከ2011 ጀምሮ ሲጫወት የነበረው የቀድሞው የሀዋሳ ከተማ፣ ባንክ እና ኢትዮ ኤሌክትሪክ ተጫዋች ግርማ በቀለ እና ከታዳጊ ቡድን በማደግ ከ2011 የውድድር ዓመት ጀምሮ በአጥቂ ስፍራ ላይ ለክለቡ ተሰልፎ ወሳኝ ግቦችን ሲያስቆጥር የነበረው ይገዙ ቦጋለ ለተጨማሪ ሁለት ዓመታት ውላቸውን ለማራዘም መስማማታቸው ታውቋል።

ሲዳማ ቡና በቅርቡ የአሰልጣኝ ዘርዓይ ሙሉ እና የረዳቶቹን ውል ለተጨማሪ ሁለት ዓመት እንዲቆዩ ማራዘሙ ይታወሳል፡፡

👉እጅዎን በተደጋጋሚ በሳሙና በአግባቡ በመታጠብ አልያም አልኮል እና ሳኒታይዘር በመጠቀም

👉ከሰዎች ጋር ንክኪ በማስወገድ

👉ከአላስፈላጊ እንቅስቃሴ በመገደብ፣ አካላዊ ርቀት በመጠበቅ እና በቤት በመቆየት ራሳችንን ከኮሮና ቫይረስ እንጠብቅ!


© ሶከር ኢትዮጵያ