ሦስት ተጫዋቾች ከቅዱስ ጊዮርጊስ ጋር አይቀጥሉም

በዝውውር ገበያው ላይ በንቃት ተሳትፎን እያደረጉ ካሉ ክለቦች መካከል አንዱ የሆነው ቅዱስ ጊዮርጊስ አዳዲስ ተጫዋቾች ከማስፈረም ባለፈ የነባሮችንም ውል እያራዘመ ይገኛል፡፡ ከዚህ በተቃራኒው ደግሞ ክለቡ ከሦስት ተጫዋቾቹ ጋር እንደማይቀጥል ተሰምቷል፡፡

የቀድሞው የሀዋሳ ከተማ፣ ሲዳማ ቡና እና ንግድ ባንክ የግራ መስመር ተከላካይ መሐሪ መና ንግድ ባንክን ከለቀቀ በኃላ ያለፉት አራት ዓመታትን በፈረሰኞቹ ቤት ቆይታን አድርጓል። በ2009 ክረምት አባጅፋርን ለቆ ቅዱስ ጊዮርጊስን ከተቀላቀለ በኋላ ወጣ ገባ አቋም ያሳየው አጥቂው አሜ መሐመድ እና የቅዱስ ጊዮርጊስ የታዳጊ ቡድን ውጤት የሆነው የመስመር አጥቂው አቡበከር ሳኒ ሌሎች ከክለቡ ጋር የማይቀጥሉ ተጫዋቾች ናቸው፡፡

👉እጅዎን በተደጋጋሚ በሳሙና በአግባቡ በመታጠብ አልያም አልኮል እና ሳኒታይዘር በመጠቀም

👉ከሰዎች ጋር ንክኪ በማስወገድ

👉ከአላስፈላጊ እንቅስቃሴ በመገደብ፣ አካላዊ ርቀት በመጠበቅ እና በቤት በመቆየት ራሳችንን ከኮሮና ቫይረስ እንጠብቅ!


© ሶከር ኢትዮጵያ