የጣና ሞገዶቹ የመስመር ተከላካያቸውን ውል አደሱ

ቡድናቸውን በማጠናከር ረገድ ጠንክረው እየሰሩ የሚገኙት ባህር ዳር ከተማዎች የመስመር ተከላካያቸውን ውል ከደቂቃዎች በፊት አድሰዋል።

የ11 ነባር ተጫዋቾችን ውል ያደሱት ባህር ዳር ከተማዎች 3 አዲስ ተጫዋቾችን ወደ ቡድናቸው ለመቀላቀል መስማማታቸው ይታወቃል። ከደቂቃዎች በፊት ደግሞ የመስመር ተከላካያቸውን ሳሙኤል ተስፋዬን ውል ለ2 ዓመታት አራዝመዋል።

ከቅዱስ ጊዮርጊስ የተስፋ ቡድን ያደገው ይህ ተጫዋች 3 ዓመታትን በፈረሰኞቹ ቤት ቆይታ ካደረገ በኋላ ዓምና ወደ ባህር ዳር ከተማ ማቅናቱ ይታወሳል። ተጫዋቹም ውሉ መጠናቀቁን ተከትሎ በዛሬው እለት ከቡድኑ ጋር ለተጨማሪ 2 ዓመታት ለመቆየት ተስማምቷል።

ሳሙኤል የኢትዮጵያ ከ17 ዓመት በታች ብሄራዊ ቡድን ውስጥ ጥሩ ግልጋሎት መስጠቱ ይታወሳል።

👉እጅዎን በተደጋጋሚ በሳሙና በአግባቡ በመታጠብ አልያም አልኮል እና ሳኒታይዘር በመጠቀም

👉ከሰዎች ጋር ንክኪ በማስወገድ

👉ከአላስፈላጊ እንቅስቃሴ በመገደብ፣ አካላዊ ርቀት በመጠበቅ እና በቤት በመቆየት ራሳችንን ከኮሮና ቫይረስ እንጠብቅ!


© ሶከር ኢትዮጵያ