ምንተስኖት ከበደ የመቐለ አራተኛ ፈራሚ ሆኗል

ምንተስኖት ከበደ አመሻሹን የአሰልጣኝ ገብረመድህን ኃይሌን ቡድን ለመቀላቀል ተስማማ፡፡

የቀድሞው የአዳማ ከተማ የመሀል ተከላካይ ያለፉትን ሦስት አመታት በመከላከያ በመጫወት ያሳለፈ ሲሆን በከፍተኛ ሊጉ ክለብ ያለው ውል በመጠናቀቁ ወደ መቐለ በአንድ ዓመት ውል አምርቷል። ከቀድሞ አሰልጣኙ ገብረመድህን ኃይሌ ጋርም በድጋሚ የሚገናኝ ይሆናል።

በትላንትናው ዕለት አማካዩን ነፃነት ገብረመድህንን በማስፈረም ወደ ዝውውሩ የገቡት መቐለ 70 እንደርታዎች እስካሁን አራት ተጫዋቾች አስፈርመዋል፡፡

👉እጅዎን በተደጋጋሚ በሳሙና በአግባቡ በመታጠብ አልያም አልኮል እና ሳኒታይዘር በመጠቀም

👉ከሰዎች ጋር ንክኪ በማስወገድ

👉ከአላስፈላጊ እንቅስቃሴ በመገደብ፣ አካላዊ ርቀት በመጠበቅ እና በቤት በመቆየት ራሳችንን ከኮሮና ቫይረስ እንጠብቅ!


© ሶከር ኢትዮጵያ