የጣና ሞገዶቹ የወሳኝ ተጫዋቻቸውን ውል አራዝመዋል

ባህር ዳር ከተማዎች ከበርካታ ክለቦች ጋር ስሙ ሲያያዝ የነበረውን ተጫዋች በቡድናቸው አቆይተዋል።

በአሰልጣኝ ፋሲል ተካልኝ የሚመሩት ባህር ዳር ከተማዎች ለቀጣይ ዓመት ውድድር ስራዎችን በንቃት እየከወኑ ይገኛሉ። በዚህም የ12 ነባር ተጫዋቾችን ውል እስከ ዛሬ ሲያድሱ 4 አዳዲስ ተጫዋቾችንም ወደ ስብስባቸው ቀላቅለዋል። ዛሬ ከሰዓት ደግሞ የወሳኙን አማካይ ፍፁም ዓለሙን ውል ለ2 ዓመታት ማራዘማቸው ታውቋል።

ለጥቁር አባይ፣ ደብረማርቆስ ዩኒቨርስቲ እና ፋሲል ከነማ መጫወት የቻለው ይህ አማካይ በያዝነው ዓመት ጉዞውነን ወደ ባህር ዳር በማድረግ ድንቅ ጊዜን አሳልፏል። በተለይ ከአጥቂ ጀርባ በሚገኝ ቦታ ላይ በመጫወት 9 ጎሎችን በሊጉ አስቆጥሮ የክለቡ የልብ ምት ሆኖ አሳልፏል። ምንም እንኳን ተጫዋቹ ከመቐለ 70 እንድርታ እና ፋሲል ከነማ ጋር በይበል ስሙ ቢያያዝም በዛሬው እለት በጣና ሞገዶቹ ጋር ለመቆየት ፊርማውን አኑሯል።

👉እጅዎን በተደጋጋሚ በሳሙና በአግባቡ በመታጠብ አልያም አልኮል እና ሳኒታይዘር በመጠቀም

👉ከሰዎች ጋር ንክኪ በማስወገድ

👉ከአላስፈላጊ እንቅስቃሴ በመገደብ፣ አካላዊ ርቀት በመጠበቅ እና በቤት በመቆየት ራሳችንን ከኮሮና ቫይረስ እንጠብቅ!


© ሶከር ኢትዮጵያ