ባህር ዳር ከተማ 4ኛ ተጫዋች ለማስፈረም ተስማማ

በዝውውር ገበያው ላይ ጠንክረው እየሰሩ የሚገኙት የጣና ሞገዶቹ ከደቂቃዎች በፊት የአማካይ መስመር ተጫዋቹ አፈወርቅ ኃይሉን ወደ ቡድናቸው ለመቀላቀል ተስማምተዋል።

ዓምና ከወልዋሎ ዓ/ዩ ወደ ሃዲያ ሆሳዕና አምርቶ ጥሩ ግልጋሎት የሰጠው አፈወርቅ ኃይሉ ለኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድንም ጥሪ ቀርቦለት መጫወቱ ይታወሳል። ተጫዋቹ ዓምና ሃዲያን ከመቀላቀሉ በፊት ለባህር ዳር ፊርማውን ለማኖር ተቃርቦ የነበረ ቢሆንም ጉዞውን ወደ ሆሳዕና ማድረጉ የሚታወስ ሲሆን ለሁለት ዓመታት ውል ወደ ባህር ዳር ለማምራት ነው ከስምምነት የደረሰው።

ባህር ዳር ከተማዎች ከዚህ በፊት የዜናው ፈረደ፣ የፍቅረሚካኤል ዓለሙ፣ የደረጄ መንግስቱ፣ የኃይለየሱስ ይታየው፣ የሚኪያስ ግርማ፣ የወሰኑ ዓሊ፣ የሳላምላክ ተገኝ፣ የሳምሶን ጥላሁን፣ የአቤል ውዱ፣ የፅዮን መርዕድ፣ የሳሙኤል ተስፋዬ እና የሰለሞን ወዴሳን ውል ለ2 ዓመታት ማደሳቸው ይታወቃል። መናፍ ዐወል፣ በረከት ጥጋቡ እና አህመድ ረሺድን ወደ ቡድናቸው ለመቀላቀል የተስማሟቸው ሌሎች ተጫዋቾች ናቸው።

👉እጅዎን በተደጋጋሚ በሳሙና በአግባቡ በመታጠብ አልያም አልኮል እና ሳኒታይዘር በመጠቀም

👉ከሰዎች ጋር ንክኪ በማስወገድ

👉ከአላስፈላጊ እንቅስቃሴ በመገደብ፣ አካላዊ ርቀት በመጠበቅ እና በቤት በመቆየት ራሳችንን ከኮሮና ቫይረስ እንጠብቅ!


© ሶከር ኢትዮጵያ