ድሬዳዋ ከተማ የቀድሞው ተጫዋቹን ለማስፈረም ተስማማ

የቀኝ መስመር ተከላካዩ ዘነበ ከበደ በድጋሚ ወደ ብርቱካናማዎቹ ለመመለስ ዛሬ ተስማምቷል፡፡

የቀድሞው የደደቢት፣ ሀዋሳ ከተማ እና ሲዳማ ቡና የቀኝ መስመር ተከላካይ ዘነበ ከበደ 2010 ላይ ሲዳማ ቡናን ከለቀቀ በኃላ ወደ ድሬዳዋ አምርቶ ሁለት የውድድር ዓመታትን በክለቡ ካሳለፈ በኃላ ነበረ በሀዋሳ፣ ሲዳማ እና ድሬዳዋ ያሰለጠኑት ዘላለም ሽፈራውን ተከትሎ ወደ መከላከያ ያመራው። ዘነበ ዘንድሮ በክለቡ ሲጫወት ቆይቶ በድጋሚ ወደ ቀድሞ ክለቡ ድሬዳዋ የሚመልሰውን የአንድ ዓመት ቅድመ ስምምነት ውል ዛሬ በመፈራረም ተስማምቷል፡፡

ድሬዳዋ ከተማዎች ዘነበ ከበደን ጨምሮ ወደ ክለቡ ለመቀላቀል የተስሟሟቸው ተጫዋቾች ቁጥርን ወደ ስድስት አሳድገዋል፡፡

© ሶከር ኢትዮጵያ


👉እጅዎን በተደጋጋሚ በሳሙና በአግባቡ በመታጠብ አልያም አልኮል እና ሳኒታይዘር በመጠቀም

👉ከሰዎች ጋር ንክኪ በማስወገድ

👉ከአላስፈላጊ እንቅስቃሴ በመገደብ፣ አካላዊ ርቀት በመጠበቅ እና በቤት በመቆየት ራሳችንን ከኮሮና ቫይረስ እንጠብቅ!